በኦሮሞ ተወላጆች ላይ እየተወሰደ ያለው የግድያ እርምጃ በወያኔ አንገት ውስጥ የገባውን ገመድ የሚያጠብቅ ነው

Aug 20, 2013 (Qeerroo) — አምባገነኑ የወያኔ ስርአት ርህራሄ ከሌለው እስራቱም አልፎ የኦሮሞን ልጆች እያደነ ይገኛል፡፡ ህወሀት ቅጥረኞቹን ተጠቅሞ በኦሮሞ ህዝብ ላይ የሚያደርገውን ኢሰብአዊ ድርጊት የወጣቶች ንቅናቄ (ቄሮ) በጥብቅ ያወግዘዋል፡፡ በኦሮሞ ወጣቶች ላይ የኦነግ ደጋፊዎች ናችሁ እያለ የሚፈፅመውን ግድያ እና እስራትም እንዲያቆም አጥብቀን እንጠይቃለን፡፡ በቅርቡ በምእራብ ሸዋ አምቦ ከተማ ውስጥ ወጣት ተስፋየ ጉታ የተባለ የኦሮሞ ልጅ ታደሰ በቀለ በተባለ የወያኔ ደህንነት በጥይት የተገደለ ሲሆን ይህ ስቃይ አሁንም እየተባባሰ በመምጣቱ ከ16 በላይ የሚሆኑ ኦሮሞዎች በአርሲ ዞን ኮፈሌ ወረዳ ውስጥ በወያኔ መንግስት ጦር ተገድለዋል፣ ቁጥራቸው ከ200 በላይ የሚሆኑት ደግሞ በእስር ቤት ውስጥ ታፍነው ይገኛሉ፡፡ ከእነዚህም መካከል፡-

 1. አደም   ጀማል
 2. ሌንጮ   ጂልቻ
 3. ሀቢብ    ዋቤ
 4. ጋቻኖ    ቱሴ
 5. ሙሀመድ ደበል ኡሴ
 6. ጀማል/አርሾ አርሲ/
 7. ሙሀመድ ኢደኦ
 8. አማን    ቡሊ
 9. ሙሀመድ ሀሰን
 10. ረሺድ    ቡርቃ
 11. አቡሽ    ኢብራሂም
 12. ማሙሽ   ኢብራሂም እና
 13. ቱኬ በሶ

የተባሉትን  ወጣቶች መንግስት ያለ አንዳች ርህራሄ በጭካኔ ገድሏቸዋል፡፡ ይህ ሁኔታ መንግስት የኦሮሞን ህዝብ ለመጨረስ የከፈተው ዘመቻ አካል በመሆኑ የወጣቶች ንቅናቄ (ቄሮ) ድርጊቱን በአፅንኦት ያወግዘዋል፡፡

የወያኔ መንግስት እየወሰደ ያለው የግድያ እርምጃ የአገዛዝ ዘመኑ እያከተመለት መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡ በምእራብ ወለጋ ጃርሶ ወረዳ ውስጥ የወያኔ የደህንነት ሀይሎች ኢፋ ይገዙ የተባለውን ወጣት የኦነግ አባል ነህ በማለት የገደለው ሲሆን በሌሎች 9 ወጣቶች ላይ የመብት ጥያቄ በማንሳታቸው ምክንያት እንደሚገደሉ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ አስተላልፎባቸዋል፡፡ እነሱም፡-

 1. ወጣት ደሱ    አለማየሁ
 2. ወጣት ፍቃዱ  ቱፋ
 3. ወጣት ወንድሙ ጉዳ
 4. ወጣት አራርሶ  ቀጀላ
 5. ወጣት ገመቺስ  በንቲ
 6. ወጣት ቢቂላ   እስራኤል
 7. ወጣት ሁሴን   መሀመድ
 8. ወጣት አባያ   ባይሳ እና
 9. ወጣት ቶሎሳ አለማየሁ

የተባሉት ሲሆኑ በእነዚህ ወጣቶች ላይ የወያኔ መንግስት የግድያ ማስጠንቀቂያ በመስጠት አስከፊ ድርጊቱን እየፈፀመባቸው ይገኛል፡፡ የወያኔ መንግስት እየፈፀመ ያለውን ግድያ፣ እስራት፣ ከትምህርት ገበታ ማፈናቀል እና ኢፍትሀዊ ውሳኔውን ለመጋፈጥ የኦሮሞ ህዝብ በጋራ መነሳት እንዳለበት ለነፃነት የሚታገለው ወጣት ሀይል ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡ የወያኔ መንግስት ከመቼውም ጊዜ የከፋ ጫና በኦሮሞ ወጣቶች ላይ እያደረሰ መሆኑ ለኦሮሞ ህዝብ ነፃነት መጎናፀፊያው ወቅት እየቀረበ መሆኑን የሚያሳይ በመሆኑ የኦሮሞ ህዝብ ከመቼውም ጊዜ በተሻለ ሁኔታ እጅ ለእጅ ተያይዞ መብቱን መጠየቅ ያለበት አሁን ነው፡፡ የወጣቶች ንቅናቄ(ቄሮ) የወያኔ መንግስት በኦሮሞ ህዝብ ላይ እየወሰደ ያለውን አስከፊ እርምጃ በማውገዝ ማንኛውንም መስዋእትነት ከፍሎ የህዝቡን መብት ለማስከበር እንደሚሰራ ይገልፃል፡፡

ትግሉ ይቀጥላል!!! ድል ለኦሮሞ ህዝብ!!!

የወጣቶች ንቅናቄ(ቄሮ)

ነሀሴ/2013

Advertisements

About GETINET DINKAYEHU

Unity of Oromo Struggle is a priority The Oromo want dignity, self-expression, and self-governance. The Oromo want their voices to be heard. The Oromo want sovereignty They want to live together at peace with their neighbors, who themselves also live in freedom exercising their own sovereignty.The struggle for independence will continue until the Oromo question gets proper and just response. A well organized liberation struggle and the spirit of Oromummaa will save the nation’s unity and identity from later day detractors. Long Live Free Oromiyaa!!Down with Colonial forces and their lackeys!!

Posted on 23/08/2013, in Uncategorized. Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s