የማፈርያው ቴዲ አፍሮ ቅዱስ ጦርነት አዋጅና የበደሌ ቢራ የንቀት ስፓንሰርነት አሁን ይለይለታል፣ይህ የቁቤ ትውልድ ነው።

By Getinet Dinkayehu

1493264_462284973877327_2080976165_nበዚህ ጉዳይ ላይ አንድ ነገር እንድል ያነሳሳኝ የዚህን ጥቁረ የአፍሪካ ሂትለር ለሆነው ምኒሊክ 100ኛ ዓመት አከባበር አስመልክቶ አዝማሪው ቴዲ አፍሮ ምኒሊክ በኦሮሞ ላይ ያደረገው ጦርነት ቅዱስ ጦርነት ነው ማለቱንና በኦሮሞ ህዝብ ላይ የተካሄደው የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ እንደ ቅድስና ተቆጥሮለት ፊንፊኔ ላይ በአንዱ የኦርቶዶክስ በተክርስትያን የገዳዩን የሚኒሊክን ፎቶ ሰቅለው ስለዘመሩለትና እንዲሁም አክራሪ አማራዎች በቴዲ አባባል ተስማምተው በማህበራዊ ድረ ገፅ ላይ እያራገቡ ባሉት ጉዳይ ላይ እነሱ በምያቁት ቛንቛ የራሰን ሃሳብ ልናገር ብዬ ነው።

እኔ እንደማዉቀው ለገደለ ሳይሆን ለተገደው ህዝብ ነው መዘከር ያለበት ነገር ግን የተገላቢጦሽ ሆነና አሁን ለተጨፈጨፈው የኦሮሞ ህዝብ ሳይሆን ለጨፈጨፈው ምኒሊክ ለዛዉም ቅዱስ በመባል እየተዘከረለት ነው ።ያለፈውን ታሪክ አታንሱ እየተባለ ላለፈው ገዳይና ጨፍጫፊ መዘከር ምን የሚሉት ፈሊጥ ነው ? ይህ የምያመለክተው እነዚህ ሰዎች በ21 ክፍለ ዘመን ዉስጥ እያሉ ነገር ግን በአስተሳሰብ እስካሁን በ19ኛ ክፍለ ዘመን ዉስጥ እየኖሩ እንደሆነ አሁን በግልፅ እየነገሩን ነው።

ቅዱስ የሚባል ጦርነት በየትኛውም አለም ላይ የለለና እስካሁን ያልሰማን ነገር ቢሆንም ዛሬ ላይ ግን ከአዝማሪው ተዲ አፍሮ ለመጀመርያ ግዘ በኦሮሞ ህዝብ ላይ ስለሆነ ብቻ የጦርነት ቅዱስ መኖሩን ሰምተናል።በርግጥ ከተራ ዘፋኝነትና ከደብተራዎች የውሸት ታሪክ ውጪ ትክክለኛ ስሃገሪቷ የፓለቲካ እዉቀትም ሆነ ምንም አይነት የታሪክ እውቀት የለለው ተዎድሮስ ካሳሁን ባለፈው ሚኒልክን የአፍሪካ ጀግና ብሎ ለሱ ከመዝፈን በተጨማሪ አሁን ላይ ደግሞ በድጋሚ ሚኒልክ በኦሮሞ ላይ ያካሄደው ጦረነት ቅዱስ ጦርነት ነው ከማለቱ ጀርባ አንድ ነገር እንዳለ ያስረዳናል። ቴዲ አፍሮ በኦሮሞ ህዝብ ዘንድ እንደ ሂትለር የሚታየውን ሚኒሊክን በኦሮሞ ላይ ያካሄደው ቅዱስ ጦርነት ነው ማለቱ የሚያመለክተው ዛሬ ላይ ስልጣንና የጦር መሳርያ በሱና በዘሮቹ እጅ ቢኖር ኖሮ ይሄኔ እነዚህ ሰዎች ነገ ወተው ልክ እንደ አያቶቻቸው የኦሮሞን ህዝብ በያዙት መሳርያ ሁሉ ከመጨፍጨፍና እስከነ ማንነቱ ከመቅበር ወደ ኋላ የማይሉ መሆናቸዉን ከማመልከቱም በተጨማሪ ለኦሮሞ ህዝብ ያለውን ስር የሰደደ ጥላቻና ንቀት ያመለክታል።

የደብተራዎችን የውሸት ታሪክ ያካተቱ ሃያና ሰላሳ መስመር በማይሞሉ ትርኪምርኪ ግጥሞች ፋሽስት ሚኒሊክን እና የቀድሞ ገዳዮችን እንደ ጀግና የምያወድስ ስለሆነ ብቻ ገዳዩን ሚኒሊክን እና መሰሎቹን በሚያመልኩ አክራሪ አማራዎች ዘንድ ያለ እውቀቱና ችሎታው እውቅናን ያተረፈው ቴዲ አፍሮ እርኩስን ቅዱስ ነው ማለቱ ባይገርምም በዚህ አፉ ግን ስለ ፍቅር ስያወራና ፍቅር ብሎ ኮንሰርት ሊያዘጋጅ መዘጋጀቱ በጣም አሳፋሪ ከመሆኑም ለላ ወደ ኦሮምያ ለመሄድ መዘጋጀቱ ደግሞ በጣም የድፍረት ድፍረት ነወ።የፍቅርን ትርጉም የማያውቅ ስለ ፍቅቅ ማውራት አይችልም ።ለነገሩ በግድ የለሽነት እያሽከከረ በአደባባይ የሰውን ነብስ አጥፍቶ አልገደልኩም ብሎ የሚክድ ሰው በግፍ ደማቸው ለፈሰሰ ሰዎች ያስባል ብሎ ማሰብ ሞኝነት ነው።

ቴዲ አፍሮ ፍቅርን ሳይሆን መርዝን ፣አንድነትን ሳይሆን ፋሽስትነትን ፣እውነትን ሳይሆን የአደባባይ ውሸትን ፣ቅንነትን ሳይሆን ስር የሰደደ ጥላቻን፣እኩልነትን ሳይሆን የበላይነትን፣ ሰላምን ሳይሆን ቅዱስ ጦርነትን በኦሮሞ ህዝብ ላይ በምያውጀው ምላሱ ፍቅር ብሎ ኮንሰርት ስያዘጋጅ ትንሽ እንኳ አለማፈሩ ያለውን ንቀት ያሳያል።

የሚገረመው ግን ቴዲ አፍሮ ለሄኒከን በደሌ ቢራ ትርፍን ሳይሆን የወደፊት ኪሳራን እና ሞትን ማትረፉ ነው። በደሌ ቢራ በኦሮሞ መሬት ላይ ሆኖ ከኦሮሞ መሬት በሚገኘው ምርት ቢራውን እያመረተ ከ85% በላይ ገቢውን ከኦሮሞ ህዝብ ላይ እያስገባ ቅዱስ ጦርነትን በኦሮሞ ህዝብ ላይ የሚያውጀውን ተዲ አፍሮን እያወቁ ማሰተዋወቃቸውን ከቀጠሉበት ለኦሮሞ ህዝብ ያላቸውን ንቀት ከማሳየቱ በተጨማሪ እራሳቸው በኦሮሞ ህዝብ ላይ ዳግም ጦርነትን እያሳወጁ እንደ ሆነና ሚኒሊክ በኦሮሞ ላይ ያካሄደውን እንደደገፉ ስለሚቆጠር በዚህ ደግሞ የሚመጣባቸውን ከባድ ዋጋ ለመክፈል እራሳቸን ማዘጋጀት የኖርባቸዋል። ከዚህ በኋላ የትኛውም የኦሮሞ ተወላጅ በደሌን በገንዘብ ሳይሆን በነፃ እንኳ በአጠገቡ እንደማያልፍ በተግባር ከማሳየትም በላይ እያስተዋወቁ ባሉት ቅዱስ ጦርነት ምክንያት ከፍተኛ ዋጋ እንደሚከፍሉ በተጨባጭ በአጭር ግዘ ውስጥ ያዩታል። የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች እንደሚባለው ምንም እንኳ በደሌ ቢራ በኦሮሞ ህዝብ ዘንድ የሚወደድ ምርታችን ቢሆንም እነሱን ካልጎዳቸው ቅዱስ ጦርነትን ማስተዋወቃቸዉን ይቀጥሉበት ። በዚህ ንቀታቸው ቅዱስ ጦርነትን ማስተዋወቁን ከቀጠሉበት ግን ወጋ ከመክፈል ጭምር ከኦሮምያ ምድር ላይ ወደው ሳይሆን ተገደው ለመውጣትም ይዘጋጁ ።ከማስታወቅያ በኋላ ግን የኦሮሞ ህዝብ በደሌ ቢራን እንኳን መጠጣት ይቅርና በምድሩ ላይ የምያይበት ትዕግስት አይኖረውም ።

ጀርመኖች ዛሬ በናዚ ሂትለር ድርጊት ያፍሩበታል እንጂ አይኮሩበትም። ቴዲ አፍሮና መሰሎቹ ግን ዛሬ ላይም ሆናቹ ከሂትለር የማይተናነስ ጭፍጨፋን በኦሮሞ ህዝብና በደቡብ ህዝብ ላይ ያካሄደዉን ሚኒሊክን ልታፍሩበት ሲገባ ጭራሽ ቅዱስ ነው በማለት ትኮሩበታላቹ ።ይህ ደግሞ በጣም ከማሳፈርም በላይ የማንነታችሁንና የጭካኔያቹን ልክ ያሳያል ።

ጀርመኖች ሂትለር የኛ ዘር ስለሆነ እሱ ያረገው ድርጊት ትክክል ስለሆነ ይቅርታ አንጠይቅም አላሉም ፤ከአዉሮፓዉያን ጋር አንድነታቸውን ያጠናከሩት ያለፈ ታሪካቸውን ክደውም አይደለም፤ አንድነታቸውን ሲገነቡና ያለፈ መጥፎ ታሪካቸውን ሲረሱ ያንን መጥፎ ታሪክ ተካክደው አልነበረም፤ የሂትለርን ጨፍጫፊነት አለባብሰውም ኣይደለም አይ አሱ አኮ ለጀርመን በሎ ነው ሊወቀስ አይገባም ሊጨበጨብለት ፣ሊዘከርለት ፣ቅዱስ ሊባል ይገባል ወይም ሂትለርን የሰጠን እግዚአብሄር ስለሆነ እናመሰግነዋለን ብለውም አልነበረም ነገር ግን ሂትለር ባደረገው ድርጊት ጀረመኖች ያለምንም ማንገራገር ነበር አይሁዶችን በአደባባይ ይቅርታ በመጠየቅ ጠላትነትትን አስቀርተው እርቅን በመሃላቸው የፈጠሩት ። የአመሪካ ነጮችም በተመሳሳይ መልኩ ነበር ጥቁሮች ላይ ዘሮቻቸው ባደረጉት በደል ይቅርታን በመጠየቅ የዛሬዋ አመሪካ ለጥቁሮችም ቤታቸው እንድትሆን ያደረጉት ። የተገላቢጦሽ ግን አክራሪ አማራዎችና ቴዲ አፍሮ እንዲሁም ዘሮቻቸው እንኳንስ አያቶቻቸው በኦሮሞ ህዝብ ላይ ላደረሱት በደል ይቅርታ መጠየቅ ይቅርና ጭራሽ ዛሬ ላይም ሆነው ትላንት የኦሮሞን ህዝብ ደም ሲያፈሱ ታሪካቸዉን እና ባህላቸዉን ስያጠፉና የራሳቸዉን በላያቸው ላይ ጭነው የኦሮሞን ህዝብ ከእነታሪኩ ለማጥፋት ዘምተዉባቸው ይህ ነው የማይባል ጭፍጨፋ ለፈፀሙባቸው አፄዎች ቅዱሱ ነው በማለት ለሱ ከመዘከር በተጨማሪ ዳግም ጦርነትን በኦሮሞ ህዝብ ላይ እያወጁ በጎን ደግሞ በውስጣቸው የያዙትን መርዝ ለማስተባበል ወይም ለመሸፈን እራሳቸውን የኢትዮጵያ ቅጥር ጠባቂ በማረግ በውሸት አንድነት ስም ስለ ፍቅር ስያወሩ ትንሽ እንዃ አያፍሩም።

ለላው አስገራሚ ነገር ደግሞ ጭራሽ በቤተክርስትያን ውስጥ ለእግዝአብሔር መስገድ ቀርቶ የእርኩስና ገዳይን ፎቶን በመስቀል በሚዘከርለት ዘመን ላይም ደረስን።የኦሮሞ ወንዶች እጅ ቆረጣ፣ የኦሮሞ ሰቶች ጡት ቆረጣ፣ የኦሮሞ ህዝብን በዘመናዊው መሳርያ መጨፍጨፍና በረሃብ የመጨረስ ዘመቻን እንደቅድስና በማየት በአንዱ የኦርቶዶክስ ቤተክሪስትያን ዉስጥ የእርኩሱን የሚኒሊክን ፎቶ ከፍ አድርጎ በመስቀል ልክ ከእግዚአብሄር እንደተላከ በመቁጠር ስዘምሩለትና የገዳዩን መቶኛ አመት ሲያከብሩ ትንሽ እንኳ ይሉኝታና እፍረት የላቸውም። ለማንኛውም የኦሮሞ ህዝብ እልቂት ቅድስና መሆኑን በግልፅ በመናገር አስረድታቹናል እኛም እናመሰግናለን። አሁን እኛም ዝም የምንልበት ጉዳይ አይደለም ። እኛ የምናዉቀው አንዲት ቤተክርስትያን ማራመድ ያለባት በህዝቦች መሃል ፍቅርና ሰላም እንዲፈጠር ማረግ እንድሁም ለፈጣሪ ክብር መስጠት እንጂ ሂትለር ከፈፀመው የዘር ማጥፋት ወንጀል የማይተናነስ ወንጀል በኦሮሞ ህዝብ ላይ የፈፀመውን ሚኒሊክን ማክበር፤ለሱ መዘመርና ለሱ ክብር መስጠት በየትም አለም ላይ ተቀባይነት የለለው ነገር ነው። ይህ የሚያመለክተው በኦሮሞ ህዝብ ላይ የተካሄደው ጦርነት ቅዱስ መሆኑን በበተክርስትያን ዉስጥ የማስተማር ሁነታ የቆየና ስር የሰደደ አስተምሮት ከመሆኑም በላይ ለኦሮሞ ህዝብ ያለውን ጥላቻና የኦሮሞ ህዝብን ለማጥፋት አሁንም በግልፅ እየተዘጋጀ ያለ ወጥመድና ተነሳሽነት እዛ አካባቢም እንዳለ ያመለክታል።

መቼም ሚኒሊክ በኦሮሞ ህዝብ ላይ የፈጸመዉን በደል አታውቁም ብየ አልገምትም። ይሄንን ታሪክ የማያውቅ ሰው ካለ ይህ ሰው የሁሉንም ታሪክ ወይንም የኢትዮጵያንም ፣የአማራውንም፣ የኦሮሞውንም ፣የደቡቡንም፣ የትግሬውንም የራሱንም ታሪክና ማንነት እንደማያውቅ ይቆጠራል ።ነገር ግን እነ እንደሚመስለኝ የታሪኩን አለማወቅ ሳይሆን እያወቁ በጥላሼት መቀባትና መቅበር፤ የውሸት ታሪክን በመፍጠር የራስን ታሪክ ደመቅ አድርጎ ማናፈስ ፤የለላውን ግን በውሸት መተካትና አሳንሶ መናገር ሲወርድ ሲዋረድ የመጣና የተለመደ አሰራር ከመሆኑም በተጨማሪ ለለላው ህብረተሰብ ጭፍን የሆነ ጥላቻና ጭካኔነት እንጂ አንዳችም ክብርና ርህራሄ እንደለላቹ የምያሳይ ነው። ለዚህ ደግሞ እምነትም አይገድባችሁም።በሀይማኖት ከለላ ውሰጥ ነው ትናንት የኦሮሞ ህዝብ ያለቀው ማንነቱ ሲረገጥ የነበረው ይህ ዛሬም ቀጥሎበታል። ከዱሮም ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ የለላው ህዝብ ማለቅ እንደ ቅድስና ሲዘፈንብንና የለለን የውሸት ታሪክ በመፍጠር ለራሳቹ ወገን የለለውን ስም በመስጠትና እላይ በመቆለል ስትሰብኩን ስንሰማ ነው ያደግነው።ዛሬም እናንተ ገዳዮቹን አፄዎቻችሁን እንደ ጀግና ስታወድሱና ስትጨፍሩብን እኛም ደግሞ የአባቶቻችን ገዳዮች እንደ ቅዱስ ሲዘመርላቸው ስጨፈርላቸው እያየን ዝም እንድንል ልትመክሩንና ልታስገድዱን የምትትፈልጉ ደፋሮች።

ሚኒሊክ ጦርነት በከፈተበት ግዜ ከኦሮሞ ህዝብ ላይ እጃቸዉንና ጡታቸዉን እያስቆረጠና እየገደለ ገደል ዉስጥ ሲጥል ከእሱ ጋር ታቦትና መስቀል ይዞ በመሄድ የኦሮሞን እልቂት የሚመርቅ የአማራ ጳጳስ አብሮት እንደ ነበረ ነው ታሪክ የሚነግረን። ዛሬም ደግሞ የሚኒሊክን ቅዱስነትን በቤተክርስትያን ዉስጥ በተግባር እያየን ነው። ያለማፈር ብዛት ግን እናንተው ሰዎች ለላዉን ጠባብና ዘረኛ ብላቹ ለመስደብ ማንም አይቀድማችሁም ።በራሳቹ አይን ያወጣ የዘር ጥላቻ ውስጥ እየዋኛቹና በዘራቹ ክልል ብቻ እየተሽከረከራቹ መሆኑን ለአለም እንዲህ በአደባባይ እያሳያቹ በእናንተ ብሶ ለላውን ዘረረኛ፣ ጠባብ ማለትና ጣት መቀሰራቹ የአስተሳሰብ ልክን ያሳያል።እንዲህ አይነት ጭፍንነትና ጨካኝነት ደግሞ የትም አያደርስም ።ጀርመኖች እንኳን ለሂትለር መዘከር ይቅርና ዛሬም ድረስ በየትኛውም ኣጋጣሚ ስለ ሂትለር ሲነሳ የሱን ክፋትና አውሬነት ሳያነሱት አልፈው ኣያውቁም ። የታሪካቸው መጥፎ አካል አንደሆነ አድርገው ይናገሩታል ፤ለትውልድም አይደብቁትም ።ይህ ነው ደግሞ አዋቂነት ይህ ነው የሰው ልጅነትን ባህሪ መላበስ ማለት ።ነፍጠኛ ግን በነፍጥ ብቻ ስለምያስብ ድሮም ሆነ ዛሬ መጥፎ ታሪኮቹ ሲነሳ አይወድም ፤ያረጉትን ስለምያቁ እንዲወራባቸውም አይፈልጉም ፤ለራሳቸው ግን አሁንም ድረስ መርዛቸውን እየረጩን ነው።ይሄ ደሞ ለኛ ለኦሮሞዎች የታሪክ መጥፎ ጠባሳችን ነውና መቼም ቢሆን አንደብቀዉም።በትክክል የሆነውን ነገር አናወራዋለን፤ ለትውልድ ሁሉ ከማስተላለፍ ወደ ኋላ የምንልበት ምንም ምክንያት የለም።እናንተ ይህንን ሳትቀበሉና ጭፍንነታቹን ሳታቆሙ ሺ ግዘ ስለ አንድነትና ስለ ፍቅር ብታወሩ ኦሮሞን ማቆም የምትችሉበት ደረጃ ላይ አይደላቸሁም።ዘመኑ 19ኛ ክ/ዘሮ ሳይሆን 21ኛ ክፍለ ዘመን ነው። አሁን ያለው የአነድነትና የፍቅር ስብከት ዉሸትና በውስጡ ገዳይ መርዝ የያዘ ስለመሆኑ ኦሮሞ ቢቻ ሳይሆን ሁሉም ህብረተሰብ አውቆታል።

ደብተራዎች በርግጥ የራሳቹን የተረተረት ታሪክ በውሸት እያደበላለቃቹ መፃፍ መብታቹ ቢሆንም ነገር ግን ይሄንን በውሸት የተጨመላለቀውን ታሪክ በኦሮሞ ህዝብ ላይ ለመጫን አንዳችም መብት እንደለላችው ማወቅም ይኖርባቹሀል።

ምንሊክ ኢትዮጵያን አንድ አደረገ ብላቹ እንደ ጀግንነት የምታወሩት ታሪክ ውሸት መሆኑን የማያውቅ የለም ብሎ ማሰብ ሞኝነት ነው።እናንተ እውነትን ደብቃቹ በውሸት ብታናፍሱም ታሪክ እንደሚናገረው ምኒሊክ በ 19ኛ ክፍለ ዘመን ዉስጥ ከአዉሮፓውያን ባገኘው ዘመናዊ የጦር መሳርያና የጦር አማካሪዎችን በመተቀም ከጦርና ጋሻ ዉጪ ምንም ባልነበረው የኦሮሞ ህዝብ ላይ ጦርነት በመክፈት ይህ ነው ተብሎ የማይገመት ከፈተኛ የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ በማካሄድ የጨረሰዉን ከጨረሰ በኋላ ሃገሩን በመቀማት መሬቱን ወስዶበት ለነፍጠኞች አሽከር እንዲሆን አስደረገ። ለሎቹ ደግሞ ለሃገር ዉስጥና ለሃገር ወጪ ገብያ በማቅረብ ባባርነት ነበር የተሸጡት።ሚኒሊክ በኦሮሞ ህዝብ ላይ ለሶስት አስር አመታት በተከታታይ ወይም ከ30 አመት በላይ ጦርነትን ያካሄደ ሲሆን በ1968-1900 መሃል ባካሄደው ጦርነት ቢቻ የኦሮሞ ህዝብ ብዛት ከ10 ሚሊዮን ወደ 5ሚኒሊዮን እንዲቀንስ አደረገ።ይህን በሪከርድ ያስቀመጡት ደግሞ ለረጅም አመታት እዛ መተው የቆዩ ዲሳንድያ የተባለው የፈረንሳይ ቄስና እንዲሁ ከሚኒሊክ ወታደር ጋር አብሮ ስሄድ የነበረና የሚኒሊክ የቅርብ ወዳጅ በመሆን ከሱ ጋር አብሮ ጦርነት ስያካሂድ የነበረው ሩሲያዊ ብላንኮቪች የሚባል ነበር።ማጂዎች በምኒሊክ ወረራ ከ90% በላይ አልቀዋል (ተገለዋል ፣ተሽጠዋል) ይህ በብዙ ታሪኮች ውስጥ የተፄፈ ነገር ነው።ግሚራዎች ከ80% በላይ አልቀዋል(ተገለዋል ብዙዎቻቸው ተሸጡ) ይሄንንም ታሪክ ፅፈው ያስቀመጡት በዛን ግዘ የአፄዎቹን ታሪክ ይፅፉ የነበሩና በአይናቸው ያዩ ነጮች ናቸው።ከፋዎች ከ75% በላይ አልቀዋል(ተገለዋል ፣ተሽጠዋል) በጥቅሉ በቁጥር ከፍተኛ የሆኑ ደቡቦችና ጋምበላዎችም በሚኒሊክ ጦርነት አልቀዋል።

ሚኒሊክ በመጠኑ ከፈተኛ የሆነ የዘር ማጥፋት ወንጀል በኦሮሞ ህዝብ ላይ ሲፈፅም የተጠቀማቸውን ዘዴዎች በተመለከተ የተወሰኑትን እንደምሳሌነት ብናነሳ፡

ከአዎሮፓ ባገኘው ዘመናዊ የጦር መሳርያና ወታደሮችን እዲሁም የጦር አማካሪ ፈረንጆችን ተጠቅሞ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኦሮሞዎችን በሚዘገንን ሁነታ ጨፈጨፋቸው።ከጦርነት የተረፉትን በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩትን የአርሲና የባሬንቱ ኦሮሞ ወንዶችን የቀኝ እጃቸዉን በማስቆረጥ የተቆረጠው እጃቸውን አንገታቸው ላይ እንዲንጠለጠል አስደረገ።የብዙ ሺ የኦሮሞ ሰቶችን ጡት እንደ ሳር አሳጨደ።በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ከብቶቻቸውን ከመዝረፉም በተጨማሪ ከብቶቻቸውን የሚጨርስ በሽታ በማሰራጨት ከብቶቹ እንድያልቁና ኦሮሞዎች በረሃብ እንዲረግፉ አስደረገ። የኦሮሞን ህዝብ በዚህ መልኩ እንዲያልቁ ካደረገ በኋላ ነፍጠኞችን በብዛት ኦሮምያ ውስጥ በማስፈር የኦሮሞን ሀገር እንዲቆጣጠሩ አስደረገ።

እንግዲ ምኒሊክ በዚህ አይነት ሁኔታ የዘር ማጥጥፋት ዘመቻን በማረግ በሃይል የኦሮሞ ህዝብንና የደቡብ ህዝብ ፡አፋር ፣ከፊቾ፣ ኩሎ ኮንታ፣ ወላይታ፣ ሀደያ፣ ሲዳማ ፣ገድዮ፣ ኮንሶ ፣ሞቻ ፣ግሚራና የተቀሩትን በመጨፍጨፍና አንድ ላይ በመጨፍለቅ በቅኝ ግዛት መልክ የአሁኗን የትዮጵያ ኢምፓየር(Ethiopian Empire) የምትባለውን መፍጠሩ ነው የምናዉቀው።ከዛ በፊት ግን የኦሮሞ ህዝብ ለብዙ ሺ አመታት የራሱ ሃገር ፣የራሱ ማንነት፣ የራሱ ባህል ና በራሱ ዲሞክራሳዊ ስርዓተ ሲተዳደር ነበር።

ኦሮሞ በራሱ ሀገር ላይ ሲኖር በነበረበት ግዘም አፄዎቹ ለረጅም አመታት የኦሮሞ ሃገርን ዳር ድንበር ሰብረው ለመግግባት በተደጋሚ ጥረት ሲያረጉ የነበረ ሲሆን ኦሮሞ ሀገሩን ሰብረው እንዳይገቡበት ሲከላከል ነበር የኖረው።የኦሮሞ ህዝብ እራሱን ለመከላከል ከለሎች ጎሮበት ሀገራትም ሆነ ባህር ማዶ በመሻገር የባእድን ጦር መሳርያም ሆነ ወታደር ፍለጋ ያልሄደ ሲሆን አፄዎቹ ግን በተቃራኒው ኦሮሞን ለመውጋትና ሀገሩን ለመቀማት ባህር ማዶ በመሻገር በብዙ ሺ የሚቆጠሩ የፖርቹጋል ወታደሮችን ከራሳቸው ጋር ብያሰልፉም ኦሮሞን ለማነበርከክም ሆነ ሀገሩን ሰብረው መግባት አልቻሉም ነበር።ነገር ግን በኋላ ላይ ኣፄዎቹ በሃይማኖት ከለላ ከውጭ ከአወሮፓውያን ላይ ባገኙት የጦር መሳርያናና ወታደር እንዲሁም የጦር አማካርዎች በመታገዝ በኦሮሞ ላይ ባካሄዱት ወራራ ከ30 አመት በላይ (1868 – 1900) ከፈጀ ጦርነት በኋላ ኦሮምያን ተቆጣጠረ።

አክራሪ አማራዎችና ቴዲ አፍሮ እንዲሁም የሚኒሊክ ተከታዮች ምኒሊክን በተመለከተ ጀግና ነው በማለት ብዙ ዉሸቶችን ማዉራትና እሱ ያረገው ጦርነት ቅዱስ ነው ማለትን ትችላላቹ ነገር ግን በተጨባጭ መሬት ላይ ያለው እውነት ምኒሊክ የኦሮሞን ሀገር በጉልበት ለመያዝ በኦሮሞ ላይ የፈፀመው በደል ናዚው ሂትለር በአይሁዶች ላይ ከፈፀመው ድርጊት የማይተናነስ ነው።

ምኒሊክ በአርሲና በባሬነቱ ኦሮሞ ላይ ያካሄደውን ብዙ ዝርዝር ውስጥ ሳልገባ አጠር ባለ መልክ ብናየው፡የሚኒሊክ ጦር ዘመናዊ የጦር መሳርያ በመያዝ በአርሲ ኦሮሞዎች ላይ በተለይ በ1886 አከባቢ ለሰባት አመታት ባደረገው ዘመቻ ላይ በምያሳዝን መልኩ ከጦር ውጪ ምንም ያልነበራቸው የአርሲ ኦሮሞዎች ኣስከፊና ዘግናኝ በሆነ ጦርነት አንደ ሳር ነበር የታጨዱት ።በጦርነቱ ላይ ሳይሞቱ የቀሩት ደግሞ ተማረኩ ።ከተማረኩም በኋላ በራስ ዳርገ የሚመራው የምኒሊክ ጦር እነዚህን ንፁሃን የአርሲ ኦሮሞዎችን በማሰለፍ በአንድ ቀን ዉስጥ ቢቻ አስራ ሁለት ሺ ሰዎችን የቀኝ አጃቸዉን በመቁረጥ ኣንገታቸው ላይ ኣንጠለጠሉ ይሄንን ታሪክ ጽፎ የሰጠው ኦሮሞ ኣይደለም ፈረንጂም ኣይደለም የሚኒሊክ የራሱ የታሪክ ጸሃፊ የነበረው ሰው ነው ።

ከዚህ አስከፊ ድርጊት በኋላ ደግሞ በድጋሚ ለሎች የተረፉ ኦሮሞዎች መቼም ዘመቻው ኣበቃለት ሃገራችንም ተወስዶብናል ብለው ወደየበታቸው ገብተው ከሰነባበቱ በኋላ የሚኒሊክ ጦር በየቀበለው በማስጠራት ጠመንጃቸዉን ኣፋቸው ላይ በመደቀንና በማስፈራራት ወስደው ኣኖሌ ላይ አሁንም ከ3000 የኦሮሞ ሰቶች ላይ ጡታቸዉን ከቢዙ ሺ የኦሮሞ ወንዶች ላይ ደግሞ ቀኝ እጃቸዉን ኣስቆረጡ ።

ለላው በምኒሊክና በአማራው ጳጳስ የተመራው ደግሞ ኣሁንም ሃያ ሺ በዘመናዊ መሳርያ የታጠቁ ወታደሮችን በማሰማራት ከጨርጨር አስከ ሜታ ጨለንቆ ድረስ ሲዋጉ የነበሩት የባረንቱ ኦሮሞዎችን አየተከላከለ ጨለንቆ ከደረሰ በኋላ የአፍረን ቀሎ ኦሮሞዎች ጨለንቆ ላይ  በኣንድነት በመሰለፍ ለሃገራቸው አንድ ያላቸዉን ነብስ ለመስጠት በቆራጥነት ቆሙ ።በዚህ ግዜም የኦሮሞዎች የጦር መሳርያ ከጦርና ጋሻ እንዲሁም ከወንጭፍ ውጪ ለላ ምንም ዘመናዊ የጦር መሳርያ ኣልነበራቸዉም ። ነገር ግን በምያሳዝን መልኩ ያለቀዉም ኣለቀና የተረፉት ተማረኩ ።በሚኒሊክ ክፉ ድርጊት የጨለንቆ ደረቅ መረት በኦሮሞ ልጆች ደም አንደ ጎርፍ ተጥለቀለቀ። የአፈሪካው ጨፍጫፊው ምኒሊክ በኣርሲ ኦሮሞዎች ላይ ያደረገውን ጭፍጨፋ በጨለንቆ ላይም ደገመው ።የተማረኩትን የኦሮሞ ልጆችን አጅ አስቆረጠ በተጨማሪም ጆሮና ኣፍንጫቸው ሳይቀር ኣሳጨደ ።ከዛም በኋላ ከሚኒሊክ ጋር የነበረው የአማራው ጳጳስ በሲመ ኣብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ብሎ የአኖሌዉን ገደል አንደመረቀው ሁሉ ኣሁንም የጨለንቆን ገደል መረቀ። ከዛ በኋላ የባረንቱ ኦሮሞ፣ኣርሲ ፣ቱለማ፣ወሎ ፣ ጉጂ፣ መጫና ለሎችም መረቱ ተወስዶበት ገባሪ ሆነ።ለሎች ተይዘው ለሃገር ዉስጥና ለውጭ ገብያ በመቅረብ ተሽጠዋል።

እስቲ ይታያቹ ይህ የጭካኔ ድርጊት ሂትለር በአይሁዶቹ ላይ ካደረሰዉ ድርጊት ያነሰ ኣይደለም። አንግዲህ የቴዲ ኣፍሮው ጥቁር ሰው ምኒሊክ ስራ ይህ ነው፤ ይሄንን ነው የቴዲ አፍሮ ምንሊክ እትዮጵያን አንድ ለማረግ የካሄደው ጦርነት ቅዱስ ጦርነት ነው ብሎ በእንቁ ጋዘጣ ላይ የተናገረው፤ለዚህ ጥቁር አውሬ ነው እንግዲ የአፍሪካ ጥቁር ሰው ጀግና ብሎ የዘፈነለት፤ይሄንን እርኩስ ነው እንግዲህ በአንዱ የኦርቶዶክስ ቤተክርስታን ውስጥ ፎቶውን ሰቅለው እንደ ቅዱስ የዘመሩለት፤ይሄንን ሰውየ ነው የአማራ ሊሂቃንና የአክራሪ አማራዎች ሚድያ (ESAT) እሱ የእናንተም ጀግና ነውና እናንተም ተቀበሉ እያሉ እየዘፈኑብን ያሉት። በርግጥ አሁን ሁሉም ነገር ለይቶላቹሃል ፤ሁሉንም በግልፅ ነገራቹን እናመሰግናለን። ከእንግዲህ ስላተነቃበት መርዛማው የአንድነት ስምና ሲለ መርዛማው የኢትዮጵያ ፍቅር እንደት ማስተባበል እደምትችሉ ወደፊት እናያለን።አሁንም የጭፍን ፖለቲካና አካሄድ ግን የትም የትም አያደርስም። ጆሮ ያለው ይስማ ይህ የቁቤ ትውልድ ነው። ቁቤ ማንነቱን የምያሳቹይበት ግዘ ነው። ያኔ በጨለማው ዘመን አያቶቻቹ በኦሮሞ ህዝብ ላይ ያደረሱትን በደል ዛረም እንደግማለን ብሎ ማሰብና በኛ ጫንቃ ላይ ሆናቹ ላለፉት ገዳዮች እየዘመርን እንኖራለን ብሎ መነሳት በጋዝ ላይ እሳትን እንደ መለኮስ ነው።ዘመኑ 19ኛ ክ/ዘመን ሳይሆን 21ኛ ክ/ዘመን ነው አራት ነጥብ

getinetdinkayehu@gmail.com

Advertisements

About GETINET DINKAYEHU

Unity of Oromo Struggle is a priority The Oromo want dignity, self-expression, and self-governance. The Oromo want their voices to be heard. The Oromo want sovereignty They want to live together at peace with their neighbors, who themselves also live in freedom exercising their own sovereignty.The struggle for independence will continue until the Oromo question gets proper and just response. A well organized liberation struggle and the spirit of Oromummaa will save the nation’s unity and identity from later day detractors. Long Live Free Oromiyaa!!Down with Colonial forces and their lackeys!!

Posted on 28/12/2013, in Uncategorized. Bookmark the permalink. Leave a comment.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s